የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ላይ የተከበሩ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በሀገሪቱ ወቅታዊ የኑሮ ውድነትና ማህበራዊ ቀውስ ዙሪያ ጠንከር ያሉ ነጥቦችን አንስተዋል።

1 / 1

1.

በምክር ቤቱ ውሎ ላይ ባደረጉት ንግግር በአሁኑ ወቅት የቤት ኪራይ ዋጋ ከአብዛኛው ዜጋ ወርሃዊ ገቢ በላይ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ደሳለኝ፣ ቀደም ሲል የነበረው መካከለኛ የህብረተሰብ መደብ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን ተናግረዋል።
በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው ህዝብ በድህነት የሚማቅቅባት የሁለት ፅንፍ መደቦች ብቻ መገለጫ እየሆነች መምጣቱን በማሳሰብ አሳሳቢነቱን ገልጸዋል። ለመሆኑ እርስዎስ በዚህ ሃሳብ ላይ ምን ይላሉ?
በአሁኑ ወቅት በአካባቢያችሁ ያለው የቤት ኪራይ ንረት እና የኑሮ ውድነት ሁኔታ በምን መልኩ ይገለጻል? ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን።