በሰላም እየመጣች ነው!

በሰላም እየመጣች ነው!

በሰላም እየመጣች ነው!

በሰላም እየመጣች ነው! 

#dialectis ሰላም ጤና ይስጥልን የተከበራችሁ የዜናችን ተከታታዮች! ዛሬ ሁላችንንም ደስ የሚል አንድ ታላቅ ብሄራዊ የምስራች ይዘንላችሁ ቀርበናል።

​የኢትዮጵያ የባህር ላይ ኩራት የሆነችውና በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ተቀስቅሶ በነበረው ቀውስ ምክንያት ለወራት በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ተቀርቅራ የነበረችው "ኤምቪ ጊቤ" (MV Gibe) መርከብ፣ በመጨረሻም ሙሉ ጭነቷን ይዛ ወደ ጎረቤት ጅቡቲ ወደብ በሰላም መጓዝ መጀመሯ ታውቋል!

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ባወጣው ወቅታዊ መረጃ መሰረት፣ የጉዞዋ ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከተለው ተቀምጧል፦

መርከቧ በአሁኑ ወቅት የኦማንን ባህረ ሰላጤ (Gulf of Oman) ቀጣና በሰላም አቋርጣ ጉዞዋን ቀጥላለች።

ካለችበት ፍጥነትና የባህር ላይ ሁኔታ አንጻር፣ መጪው June 28 ቀን 2026 ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ መዳረሻዋ ወደሆነው የጅቡቲ ወደብ ትገባለች ተብሎ ይጠበቃል።

MV ጊቤ የኢትዮጵያውያን የክብር መገለጫ ስትሆን፣ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 347 ዓለም አቀፍ የወደብ መዳረሻዎች ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በኩራት ከሚያውለበልቡ መርከቦቻችን መካከል አንዷ ናት።

የቀጣናው አለመረጋጋት በፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ሆነው ስራቸውን ያከናወኑት መርከበኞች ትልቅ አክብሮት ተችሯቸዋል።

በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ የነበረውን የደህንነት ስጋትና የእለት ተእለት አስፈሪ ውጥረት በከፍተኛ ሙያዊ ስነ-ምግባርና ጽናት በመቋቋም፣ የሀገራቸውን ብሄራዊ ክብር አስጠብቀው ለዚህ ያበቁት የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ መርከበኞች ታላቅ ምስጋና ሊሰጣቸው ይገባል።

መርከቧ በሰላም ወደ መዳረሻዋ እንድትደርስና ቀጣይ ስራዎቿን እንድታከናውን መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።

#Via የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት