በኢትዮጵያ ቱሪዝም ለምን “አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር” ተባለ? የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማብራሪያ
በኢትዮጵያ ቱሪዝም ለምን “አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር” ተባለ? የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማብራሪያ
1.
በኢትዮጵያ ቱሪዝም ለምን “አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር” ተባለ? የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማብራሪያ
ዘርፉ ለሀገሪቱ ያለውን ፋይዳ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል፦
-
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ እስከ 12.6 ትሪሊዮን ዶላር የሚንቀሳቀስበት ዘርፍ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ከዚህ ታላቅ ሀብት የድርሻዋን እንድታገኝ ያደርጋል።
-
በዓለም ላይ ከ370 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሚቀጠሩበት ዘርፍ ሲሆን፣ በሀገር ውስጥ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ትልቅ አቅም አለው።
-
ቱሪስቶች በቀጥታ ከሚያደርጉት ግዢ በመነሳት ከአነስተኛ የሀገር ውስጥ ቢዝነሶች (እንደ ቡና ማፍላት) ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) ድረስ ሰፊ ትስስር ይፈጥራል።
-
ኢትዮጵያ "ያልተገዛች ሀገር" በመሆኗ ብቻ ስሟ በረሃብና በችግር እንዲታወቅ ሆን ተብሎ የተሰራባትን የተሳሳተ ትርክት (Narration) ቱሪስቶች መጥተው እውነታውን ሲያዩ እንዲቀየር ያደርጋል።
መንግሥት በቱሪዝም ላይ የሚያወጣው ወጪ የሚባክን ሳይሆን፣ የሀገሪቱን ገጽታ በመቀየር ለሌሎች ዘርፎች ጭምር መነቃቃትን የሚፈጥር ስትራቴጂካዊ ውሳኔ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
ዲያሌክቲክሰ ሚዲያ