በቁጥጥር ስር የዋለው 900 ሊትር ቤንዚንና አደንዛዥ ዕፅ፦ በለሚ ኩራ የመኖሪያ ቤቶችን የሽብርና የሺሻ መሸሸጊያ ያደረጉ

በቁጥጥር ስር የዋለው 900 ሊትር ቤንዚንና አደንዛዥ ዕፅ፦ በለሚ ኩራ የመኖሪያ ቤቶችን የሽብርና የሺሻ መሸሸጊያ ያደረጉ

ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ አበባ፦ በሰው መኖሪያ ቤት ውስጥ ከ900 ሊትር በላይ የሚቀጣጠል ቤንዚን ማከማቸትና አካባቢውን ለአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎች መሸሸጊያ ማድረግ የሰፈርን ሰላም ብቻ ሳይሆን የነዋሪዎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ከባድ ወንጀል ነው።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው "ወሰን" በተባለ አካባቢ፣ ይህንን መሰል አደገኛ ህገ-ወጥ ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል። መጠነ ሰፊው ኦፕሬሽን የተከናወነው የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት (NISS) እና ከፌደራል ፖሊስ ኢንተለጀንስ ጋር በጋራ በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃ ነው።

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ሚስጥራዊ ጥቆማ መሰረት፣ በአካባቢው በሚገኙ ሆቴሎችና በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በቡድን በመሰባሰብ አደንዛዥ ዕፅ እና ሺሻ በሚጠቀሙና በሚያስጠቅሙ አካላት ላይ ያተኮረ ጥናት ሲደረግ ቆይቷል።

በዚህም መሰረት ከፍርድ ቤት በተገኘ የመበርበሪያ ትዕዛዝ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የሚከተሉት እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፦

  • ተቀጣጣይ ነዳጅ፦ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ከ900 ሊትር በላይ ቤንዚን፣

  • የሺሻ ዕቃዎች፦ በርካታ የሺሻ መጠቀሚያ ገመዶች፣ መለዋወጫዎች (መዋስልሶች) እና ቡሬዎች፣

  • ዕጾችና መድኃኒቶች፦ በርካታ የትራማዶል (Tramadol) እና የማኮን መድኃኒቶች፣ እንዲሁም ሲጋራዎች፣

  • ሌሎች፦ የሲጋራ ማስታወቂያ የተለጠፈባቸው ቲሸርቶች።

#via  Addis Ababa Polic