ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ኪሮስ ዲሞክራቲክ ፓርቲን ለመወከል በኮሎራዶ ግዛት በተደረገ የአካባቢ ቅድመ ምርጫ አሸንፋለች።
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ኪሮስ ዲሞክራቲክ ፓርቲን ለመወከል በኮሎራዶ ግዛት በተደረገ የአካባቢ ቅድመ ምርጫ አሸንፋለች።
1.
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ኪሮስ ዲሞክራቲክ ፓርቲን ለመወከል በኮሎራዶ ግዛት በተደረገ የአካባቢ ቅድመ ምርጫ አሸንፋለች።
ዲሞክራቲክ ሶሻሊስቷ ሜላት ኪሮስ ዲሞክራቲክ ፓርቲን ለመወከል በኮሎራዶ ግዛት በተደረገ የአካባቢ ቅድመ ምርጫ አሸንፋለች።
ትናንት ማክሰኞ በተካሄደው ምርጫ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉት ዲያና ደጌትን ማሸነፍ ችላለች። የሜላት ማሸነፍ ፓርቲው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ካስመዘገባቸው ድሎች አንዱ እንደሆነ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን በስፋት ዘግበዋል። ሜላት የዲሞክራቲክ ፓርቲው ይፋዊ ዕጩ የሆነች ሲሆን፣ በቀጣይ ከሪፐብሊካን ዕጩ ጋር ትወዳደራለች። ካሸነፈችም የተወካዮች ምክር ቤት ትገባለች።
ባለፈው ሳምንት በኒው ዮርክ በተካሄደ ምርጫ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ ሁለት ዴሞክራቲክ እንደራሴዎችን በሌሎች ዕጩዎች ተተክተዋል።
በስምንት ቀናት ውስጥ ከምክር ቤት አባል እንደራሴ ጋር ተፎካክራ ምርጫ ያሸነፈች ሦስተኛዋ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩ መሆኗን ሲኤንኤን ዘግቧል። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ኪሮስ በቀጣይ ዓመት ኅዳር ላይ በሚደረግ ምርጫ የምትወዳደር ይሆናል። የ29 ዓመቷ ሜላት በአውሮፓውያኑ 2022 ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ኖተር ዳም በሕግ ተመርቃለች።
ዲያሌክቲክሰ ሚዲያ