ማርክሰ ' ና ጄኒቮን

ማርክሰ ' ና ጄኒቮን

ማርክሰ ' ና  ጄኒቮን
: :

ማርክሰ ' ና  ጄኒቮን

ማርክሰ ' ና  ጄኒቮን ካርል ማርክሰ ጋዜጠኛ : ሶስዬሎጂሰት ኢኮኖሚሰት : ፓለቲካል ሳይንቲሰት ደራሲ ሀያሲና ኮምዩኒሰት የነበረ ጀርመናዊ ነው። ራይንዘይቱንግ የተባለ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሳለ ሶሻሊሰታዊ ፅሁፎቹን እንዲተው የጀርመን መንግሰት ደጋጋሚ ማሰጠንቂያዎችን ሰጥ ቶት ነበር - በጄ አላለም ።ጋዜጣዋ ታገደች ። መታገዷን ባወቀ ጊዜ ማተሚያ ቤት ሄዶ ምነው ሲል ጮኸ ።

አላሰቀምጥ ቢሉት ወደ ቤልጂየም ተሰደደ። ቤልጂየምም ውጣልኝ አለችው ። ወደ ፈረንሳይ አቀና ። ፈረንሳይም እምቢኝ አለች ። የመጨረሻ ማረፊያው እንግሊዝ ለንደን ሆነች ።

ማርከሰ በሰደት ሳለ ለዶክትሬት ዲግሪው የፃፈውን የጥናት ወረቀት ለቦን ዩኒቨርሲቲ ፕረፌሰሮች ላከው ።  አንድ ጊዜ አንብበውት መጥተህ ዶክትሬትህን ውሰድ ነበር ያሉት ። ለዲፌንሰ እንኳ አልቀረበም ። በተሰደደበት ሀገር ሁሉ ኮምዩኒሰታዊ የጥናት ቡድኖ ችን : የፓርቲ ህዋሶችን ያደራጅ ነበር ።  ሚሰቱ ጄኒ ቮን ዌሰትፋለን የንዑሰ ከበርቴ ልጅ ነች ። ከወላጆቿ ኮምዩኒሰት ለምን ታገቢያለሸ ጫና ነበረባት ። እሷ የቲያትር ሀያሲ እሱ ደሞ ንፁህ ኮምዪኒሰት ።

ጄኒ ማርክሰን '' ሌላ ሰራ እየሰራህ ብንኖር አይሻልም ? ችግሩ በረታ እኮ ሰትለው ' አይ !  መፅሀፌ ሲታተም ያኔ ደህና ኑሮ እንኖራለን ይላት ነበር ። ልጆቻቸው በም ግብ እጥረት ይሞቱባቸው ጀመር ።  ሚሰቱ ጄኒም በምግብ እጥረት ህይወቷ አለፈ ። ማርክሰ ሀዘኑ ቢበረታበትም ከአላማው ንቅንቅ አላለም ነበር  ። ጄኒ በህይወት ሳለች ባሏ በሄደበት ሁሉ ተንከራታለች ። የባለፀጋ ልጅ ሆና እሱን አሱን ሰትል ለፍቅር  ሰትል የከፈለችው ንፁህ ዋጋዋ ሞቷ ነበር ። የኢትዮጸያ ሴቶችም የጄኒን ነገር ልብ ይበሉ ።

ማርክሰ በለንደን ሙዚየም ቤተመፅሀፍ በቀን ለ 18 ሰአታት  ያህል ያነብ ነበር ።  የቤተመፅሀፉ የሚዘጋበት እኩለ ሌሊት ሰአት ሲደርሰ ደወል ይ ደወላል ።  ሌሎቹ ይወጣሉ እሱ ግን ንቅንቅ የለም ።  የቤተ መፅሀፉ ሰራተኞች መጥረጊያ ይይዙና አጠገቡ ሲደርሱ ወለሉን እየጠረጉ  አቧራ ያሰነሱበታል - ወይ ፍንክች ያባቢለዋ ልጅ ።  በመጨረሻም የፀጥታ ሰራተኞች ተጠርተው እየገፈ ታተሩ ያሰወጡታል ። ማርክሰ ከንባብ ብዛት አቅሉን እየሳተ ይወድቅ ነበር ተብሎ ተፅፎአል ።  18 አመት የፈጀው መፅሀፉ 'ዳስ ካፒታል ' ታተመ።  በዚህ መፅሀፉ ብቻ አለምን ለሁለት ገመሳት - ካፒታሊዝም ወዲህ ሶሻሊዝም ወዲያ ።

ምነዋ ጄኒ ቮን ዌሰትፋለን ይኸን ሁሉ ቆማ ባየች በነበር ።  ማርክሰ በተወለደ በ65 አመቱ በ 1883 በለንደን ህይወቱ አለፈ ። እኔምለው በአሁኗ አለም ማርክሰን የሚያክል ከሳቴ ብርሀን ይኖር ይሆን ?  እንጃ !