ስታርት አፕ ለስራ እድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ ነው

ስታርት አፕ ለስራ እድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ ነው

ስታርት አፕ ለስራ እድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ ነው

ስታርት አፕ ለስራ እድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ገለፁ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ የስታርት አፕ ስነ ምኅዳሩን ማስፋት የሚያስችል የክህሎት ልማት እና አዳዲስ የስራ ዕድል ፈጠራን የሚያበረታቱ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች የሚወዳደሩበት "ብሩህ ኢትዮጵያ" የክህሎት ውድድር ሀገራዊ ልማትን የሚያሳልጥና ስታርት አፖችን ማፍራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ባለፉት አራት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1 ሺህ 350 የፈጠራ ሀሳብ ላላቸው ዜጎች እውቅና ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚኖረውን ፋይዳ አሟጦ ለመጠቀም አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብ ላላቸው ስታርት አፖች የመስሪያ ቦታ፣ የፋይናንስ፣ የአቅም ግንባታና ሌሎች ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡