የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ. የመደበኛ ምዝገባ በሰባት ቀናት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀቀ
የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ. የመደበኛ ምዝገባ በሰባት ቀናት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀቀ
የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ. የመደበኛ ምዝገባ በሰባት ቀናት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀቀ
60,000 ሯጮችን የሚያስተናግደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ባለው ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት በግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚደረገው የምዝገባ ጊዜ እያጠረ መጥቷል።
በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ካለው ከፍተኛ ምላሽ የተነሳ በባንክ ኦፍ አሜሪካ የስያሜ አጋርነት የሚቀርበው የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. መደበኛ ምዝገባ ተጠናቋል።
ከማክሰኞ እስከ ማክሰኞ የዘለቀው የሰባት ቀናት የምዝገባ ጊዜ ውድድሩ ከተጀመረበት 1994ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት የ26 ዓመታት ታሪክ ውስጥ አጭሩ የምዝገባ ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል።
የዘንድሮው ምዝገባ ይበልጥ የቀለለው ግለሰቦች በቴሌብር (telebirr) መተግበሪያ በኩል በመጠቀም እና ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በሆነ የምዝገባ ሂደት ነው። ነፃ የውድድር ምዝገባ፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች ገቢ ማሰባሰብ እና የሰዓት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር በተደረገው አጋርነት የመጡ አዳዲስ ስኬቶች አንዱ ተደርጎ ተወስዷል።
ለዘንድሮው ውድድር ከተዘጋጁት ጠቅላላ 60,000 ቦታዎች ውስጥ 3000 የሚሆኑት ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለሚወስዱ ተማሪዎች በነፃ የሚሰጡ ሲሆን፣ ይህም አጋርነቱ ሰፊ የኅብረተሰብ ክፍል በውድድሩ ላይ እንዲሳተፍ ለማድረግ ያለውን ዓላማ የሚያሳይ ነው።
በተጨማሪም በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመረጡ ሦስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገቢ ለማሰባሰብ የታለመውን ‘ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ’ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ በጥቅምት ወር 2019ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ይጀመራል። ቀሪ ጥቂት የምዝገባ አማራጮች የዚሁ ዘመቻ አካል ለሆኑት እና ለሽያጭ ከሚቀርቡት የበጎ አድራጎት ቦታዎች ላይ ይደረጋል።
ሁሉም የበጎ አድራጎት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ሲያዙ፣ ውድድሩ በአጠቃላይ 60,000 ተመዝጋቢዎች ይኖሩታል።
Via - GreatEthiopianRun
What's Your Reaction?
Like
1
Dislike
1
Love
1
Funny
0
Wow
0
Sad
0
Angry
0
Comments (0)